ሰመራ ዩኒቨርሲቲ ለፈተና አስፈፃሚዎች የጉብኝት ፕሮግራም አዘጋጀ።

  • Home
  • ሰመራ ዩኒቨርሲቲ ለፈተና አስፈፃሚዎች የጉብኝት ፕሮግራም አዘጋጀ።
ሰመራ ዩኒቨርሲቲ ለፈተና አስፈፃሚዎች የጉብኝት ፕሮግራም አዘጋጀ። admin June 16, 2023

ሰመራ ዩኒቨርሲቲ ለፈተና አስፈፃሚዎች የጉብኝት ፕሮግራም አዘጋጀ።

ሰመራ ዩኒቨርሲቲ ለፈተና አስፈፃሚዎች የጉብኝት ፕሮግራም አዘጋጀ።

ሰመራ ዩኒቨርሲቲ ለፈተና አስፈፃሚዎች የጉብኝት ፕሮግራም አዘጋጀ።
====================================
ሰመራ ዩኒቨርሲቲ፡ ጥቅምት 05/2015 እ.ኢት.አ

ሰመራ ዩኒቨርሲቲ የ2014/2015 የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ እና የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና ለማስፈፀም ለመጡ ፈተና አስፈፃሚዎች፣ መምህራን፣ ሱፐርቫይዘሮች፣ሁሉምን የፈተና ግብረ-ሃይሉን ያካተተ ጉብኝት በማዘጋጀት የተመረጡ የአፋር ክልል ቦታወችን አስጎብኝቷቸዋል፡፡

ዛሬ ጠዋት የግብረ-ሀይሉ ጉብኝት የተጀመረው ከሰመራ ከተማ በ25ኪ.ሜ ርቀት ላይ የሚገኘውን የ’አላሎበድ’ የተፈጥሮ የፍልውሃ እንፋሎትን በማየት ሲሆን፣ ከሰአት በኋላ ደግሞ የ”ተንዳሆ ግድብን” ጎብኝተዋል።

የዚህ ጉብኝት አላማ ሰመራ ዩኒቨርሲቲ ከአራቱም የሀገሪቱ አቅጣጫዎች ፈተና ለማስፈፀም የተሰባሰቡ እንግዶቹን በዚህ አጋጣሚ ሀገራቸውን እንድያውቁ፣ ድንቅ የተፈጥሮ መስህቦችን እንዲያደንቁ እና በህሊናቸው ትዝታን ለማኖር በማሰብ ነው።

ምክንያቱም ቱሪዝም ለሰመራ ዩኒቨርሲቲ አንዱ የልህቀት አቅጣጫው በመሆኑ ዘርፉን በተግባር ለማስተዋወቅና ጥናትና ምርምር ለመስራት ለሚሹ ምሁራን በር ከፋች እንድሆንም በማለም መሆኑ ተገልጿል።
============================
የህዝብና አለምአቀፍ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት
ማህበረሰቡን እናገለግላለን!!

Write a comment
Your email address will not be published. Required fields are marked *