

ለሁለተኛው ዙር የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ተፈታኝ ተማሪዎች አጠቃላይ የፈተናው መመሪያ (Orientation) ተሰጠ።
========================================================================
ሰመራ ዩኒቨርሲቲ፡ ጥቅምት 07/2015 ዓ.ም
የ2014/2015 የሁለተኛ ደረጃ ማጠናቀቂያ እና የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና ለሚወስዱ የተፈጥሮ ሣይንስ ትምህርት ተማሪዎች አጠቃላይ የፈታ አሰራር የተመለከተ ማብራሪያ (Orientation) ተሰጠ።
ማብራሪያውን የሰጡት ከትምህርት ሚኒስተር የተወከሉ የፈተና አስፈፃሚ አካላት፣ ፈታኝ መምህራን እና የፈተና አስተባባሪ ናቸው።
ይህ የሁለተኛ ደረጃ ማጠናቀቂያ እና የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና ተማሪዎች 12 አመት የለፉበትን እና ቤተሰብ የደከመበትን ትምህርታቸውን ወደ ቀጣይ ደረጃ የሚሸጋገሩበት ድልድይ መሆኑን በመገንዘብ በተረጋጋ እና በጥንቃቄ በመስራት ጥሩ ውጤት እንዳመጡ ሁሉም አካላት በተሰጠው የስራ ዘርፍ በትጋት እንደሚሰራ ተብራርቷል።
መልካም እድል!!
=======================================================================
ህዝብና አለምአቀፍ ግንኙነት ዳይሬክቶት
ማህበረሰቡን እናገለግላለን!!