በ2015 ዓ.ም ሰመራ ዩኒቨርሲቲ የ”Remedial” ፕሮግራም ለመከታተል የተመደባችሁ ተማሪዎች በሙሉ:
በ2015 ዓ.ም የአቅም ማሻሻያ (Remedial) ፕሮግራም ለመከታተል ሰመራ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ ተማሪዎች ወደ ግቢ መግቢያ ቀናት ከመጋቢት 04-05/2015 ዓ.ም ሲሆን ምዝገባ የሚካሄደው ከመጋቢት 07-08/2015 ዓ.ም እንዲሁም ትምህርት የሚጀመረው መጋቢት 11/2015 ዓ.ም መሆኑን አውቃችሁ በተጠቀሱት ቀናት ተገኝታችሁ እንዲትመዘገቡ እየገለፅን:
በምዝገባ ወቅት:-
1. የ8ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ሰርቲፊኬት ዋናውንና ፎቶ ኮፒ
2. የ10ኛ እና የ12ኛ ክፍል ሰርቲፊኬት ዋናውንና ፎቶ ኮፒ
3. ከ9-12 ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውንና ፎቶ ኮፒ
4. ስምንት 3/4 የሆነ ጉርድ ፎቶ ግራፍ
5. የግል መገልገያ ቁሳቁሶች ማለትም፡- አንሶላ፤የትራስ ልብስ፣የስፖርት ትጥቅ አሟልታችሁ እንዲትገኙ እናሳውቃለን።
ማሳሰቢያ፡-
ከተጠቀሱት ቀናት ቀድሞም ሆነ ዘግይቶ የሚመጣን ተማሪ ዩኒቨርሲቲው የማያስተናግድ መሆኑን እየገለፅን፣ ለተጨማሪ መረጃ በዩኒቨርሲቲው ድረ-ገፅ (www.su.edu.et የምናሳውቅ መሆኑን ለመግለፅ እንወዳለን፡፡
የሰመራ ዩኒቨርሲቲ
ሬጅስትራርና አልሙናይ ዳይሬክቶሬት